“የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያበሰረ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

8

“የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያበሰረ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ባለፉት የለውጥ ዓመታት በክልሉ ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመዘገቡ ለውጦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቢሮ ኀላፊው እንዳሉት ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በስንዴ፣ አረንጓዴ አሻራ ልማት እና ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግባለች።

በለውጡ ዓመታት በትኩረት ከተከናወኑ ጉዳዮች ውስጥ የታላቁ የኢትዮጵያን ሕዳሴ ግድብ አንዱ እንደነበር ገልጸዋል። ግድቡ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያበሰረ፣ ከድህነት ለመውጣት የጀመረችውን ልማትም ያሳየ መኾኑን ገልጸዋል።

የዓባይ ግድብ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለሚደረገው ሽግግር ከፍተኛ አቅም የፈጠረ፣ የኢትዮጵያውያንን አንድነት ያሳዬ እንደኾነም አንስተዋል።

አማራ ክልል የአብላጫው የዓባይ ተፋሰስ መገኛ በመኾኑ ግድቡን ከደለል ለመከላከል በየዓመቱም በበጋው ወራት የአፈር እና ውኃ እቀባ ሥራ፣ በክረምቱ ወራት ደግሞ ተራሮችን በችግኝ የማልበስ ሥራ እየተሠራ መኾኑንም አብራርተዋል። የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ እና እንክብካቤ ሥራው በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ቦንድ ለልጆቼ እና ለልጅ ልጆቼ ያወረስኩት ታሪክ ነው” የ80 ዓመት እድሜ ባለጸጋው አባት
Next articleየወሰዱት የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ለመደበኛው የትምህርት ሂደት እንደሚያግዛቸው ተማሪዎች ተናገሩ።