“ቦንድ ለልጆቼ እና ለልጅ ልጆቼ ያወረስኩት ታሪክ ነው” የ80 ዓመት እድሜ ባለጸጋው አባት

10

ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኩረ ምዕመናን ኪዳኔ ኃይሌ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪ ናቸው። በራሳቸው፣ በልጆቻቸው እና በልጅ ልጆቻቸው ስም ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ ሲገዙ የቆዩ አባት ናቸው።

የዘመናት ቁጭት የኾነው ዓባይ ሊገደብ እንደኾነ ሲሰሙ የተሰማቸው ስሜት እንደ ትናንት እንደሚታወሳቸው ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

አያቶቼ በዓደዋ ላይ ተሳትፈው ጦርነቱን በድል አጠናቅቀዋል የሚሉት እኒህ አባት እኔ ደግሞ የእነሱ የልጅ ልጅ በመኾኔ ወቅቱ በሚጠይቀው የኔ ትውልድ ዓደዋን ምልክት ቦንድ በመግዛት ኀላፊነቴን ስወጣ ቆይቻለሁ ነው ያሉት፡፡

የሕዳሴ ግድቡ የአንድነት ኃይል የተገለጠበት ታሪክ በመኾኑ የዚህ ታሪክ አካል እንዲኾኑ በማሰብ ለልጆቻቸው እና ለልጅ ልጆቻቸው ቦንድ መግዛታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ “ቦንድ ለልጆቼ እና ለልጅ ልጆቼ ያወረስኩት ታሪክ ነው” ብለዋል።

በራሳቸው ስም የ170 ሺህ ብር ቦንድ፣ ለ20 ልጆቻቸው እና ለ20 የልጅ ልጆቻቸው ደግሞ ለእያንዳንዳቸው የ2 ሺህ ብር ቦንድ መግዛታቸውን ገልጸዋል።

ለዓመታት በንግድ ሥራ የተሠማሩት እኒህ አባት ለልጆቼ ፎቅ አልገነባሁም ብለዋል። የዚህ ታላቅ ታሪክ አካል እንዲኾኑ የሚያስችላቸውን ቦንድ ግን ገዝቼላቸዋለሁ ነው ያሉት።

አሁን በ80 ዓመታቸው መዳረሻ ላይ የሚገኙት በኩረ ምዕመናን ኪዳኔ ዕድሜ ተሰጥቶኝ ግድቡ ሲጠናቀቅ በማየቴ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

በኩረ ምዕመናን ኪዳኔ በከተማው በሚገኙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይም በመሳተፍ በከተማ አሥተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት እውቅና የተሰጣቸው አባት ናቸው፡፡

ዘጋቢ፦ገንዘብ ታደሰ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የአማራ ሴቶች ማኅበር ገለጸ።
Next article“የታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያበሰረ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)