
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) ሱዳን በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ተቋርጦ የነበረው የሦስትዮሽ ድርድር እንደገና እንዲጀምር ጥሪ አቅርባለች፡፡
በሕዳሴ ግድቡ አሞላል እና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ ሦስቱ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ውዝግብ ውስጥ ገብተው በድርድር ቆይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የድርድር ሂደቱ የኢትዮጵያን ጥቅምና ሉዓላዊነት የሚጋፋ በመሆኑ ኢትዮጵያ ድርድሩን አቋርጣለች፡፡
የሱዳኑ የመስኖ እና ውኃ ጉዳዮች ሚኒስትር ደግሞ ለግብጽ እና ለኢትዮጵያ አቻቸው ድርድሩን እንደገና እንዲጀመር እና የሦስቱን ሀገራት ፍላጎት በጠበቀ መልኩ አጥጋቢ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል ሲል ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሱዳን ከዚህ በፊት ባደረጓቸው ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶች በግድቡ ጉዳይ የሦስትዮሽ ውይይቱን ለማስቀጠል መስማማታቸውም ይታወሳል።
በደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡