የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሪፎርሙ ጠንካራ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ማኅበራትን ለመፍጠር አግዟል።

2

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሪፎርሙ ጠንካራ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች ማኅበራትን ለመፍጠር አግዟል።

አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2017 ዓ.ም የተግባር አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም የዕቅድ ግምገማ መድረክ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ በኅብረት ሥራ ዘርፍ እየተካሄደ ያለው ሪፎርም ማኅበራትን ጠንካራ እና ተወዳዳሪ እያደረገ ነው ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመሠረታዊ ማኅበራት ቁጥር 89 ሺህ 161 ደርሷል ነው ያሉት። የመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራትም በ423 ዩኒየኖች መደራጀታቸውን ገልጸዋል።

ፌዴሬሽኖች፣ ዩኒየኖች እና መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ጠቅላላ ካፒታላቸው ከ55 ቢሊዮን ብር በላይ እንደደረሰም ተናግረዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የገንዘብ ቁጠባ እና የብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ያሉት ኮሚሽነሩ ከ56 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ቁጠባ እንዳላቸውም አንስተዋል።

ኅብረት ሥራ ማኅበራት ባላቸው ተደራሸነት ልክ የበለጠ በማጠናከር ወጣቶችን እና ሴቶችን ማደራጀት፣ የሥራ ፈጠራ እሴትን በመጨመር ገበያን ማረጋጋት ላይ ሚናቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ተመስገን ዳረጎት

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ
Next articleበሕዳሴው ግድብ ላይ የታየው የአንድነት መንፈስ በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይም ሊደገም ይገባል።