
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) የቀድሞው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በድጋሚ በቃል አቀባይነት ተሹመዋል፡፡
ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት በአምባሳደርነት ያገለገሉት ዲና ሙፍቲ ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ከወጡ በኋላ በኬንያ እና ግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፤ በቅርቡ ደግሞ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል፡፡
አብመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ አምባሳደር ዲና በድጋሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሹመዋል፡፡