በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በ10 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ያገገምም ሆነ ሕይወቱ ያለፈ ሰውም የለም፡፡

187

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በ10 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ያገገምም ሆነ ሕይወቱ ያለፈ ሰውም የለም፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 172 የላቦራቶሪ ምርመራ በ10 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች የተገኙትም ዘጠኝ ከመተማ አስገድዶ ለይቶ ማቆያ እና አንድ ደግሞ ከወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ የሕክምና መስጫ ማዕከል ነው፡፡

በአማራ ክልል እስከ ዛሬ ሰኔ 2/2012 ዓ.ም ድረስ ለ3 ሺህ 327 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ተደርጎ በ129 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ ምንም ያገገመ ሰው የለም፤ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ከክልሉ አምስት ተጨማሪ ሰዎች ማገገማቸውን ያመላክታል፤ የክልሉ የጤና ቢሮ መረጃ ግን ከትናንት ወዲህ ያገገመ ሰው አለመኖሩን አመልክቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ግን በክልሉ ቫይሱ ተገኝቶባቸው የነበሩ 28 ሰዎች አገግመዋል፡፡

ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በክልሉ ለይቶ ሕክምና መስጫ ማዕከላት የሚገኙት ሁሉም ሰዎች በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡ ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል የገባ ታማሚ አለመኖሩንም ቢሮው አስታውቋል። እስካሁን በክልሉ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ ሰው የለም፡፡

በክልሉ ቫይረሱ የተገኘባቸው ከምዕራብ ጎንደር ዞን (106) (ይህ አካባቢ ከሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያውያን በለይቶ ማቆያ የሚቆዩበት ነው)፣ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን (አንድ)፣ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር (ሦስት)፣ ከደሴ ከተማ አስተዳደር (ሁለት)፣ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር (አራት)፣ ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር (ሦስት)፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን (ሁለት)፣ ከሰሜን ወሎ ዞን (አምስት)፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን (አንድ)፣ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር (አንድ) እና ከምሥራቅ ጎጃም ዞን (አንድ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) መሆናቸው ተገልጿል።

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleከባሕር ዳር አነስተኛ የንጹሕ መጠጥ ውኃ 38 በመቶው ይባክንባታል፡፡
Next articleአምባሳደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆኑ፡፡