የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት፦

10

ነሐሴ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቦረና በነበረን ቆይታ የቦረና አርብቶ አደሮችን ደስታ አየን!

 

የዝናብ እጥረት በተደጋጋሚ በድርቅ እንዲፈተን አድርጎት የነበረው የቦረና ዞን በአዲስ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

 

በዞኑ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔን ለማበጀት በተጀመረው ፊና ፕሮጀክት 14 ግድቦች መገንባታቸው የአርብቶ አደሮችን የውኃ እና የመኖ እጥረት እንዲቀረፍ ማስቻሉን ተመልክተናል፡፡

 

ፊና ውኃን፣ መሬትን፣ ግጦሽን ማሥተዳደር እና ከሕይወት ጋር አያይዞ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጡ ማስቻል ነው፤ ይህንን ደግሞ የቦረና ሕዝብ በተግባር ማሳየት ችሏል፡፡

 

ዛሬ የቦረና አርብቶ አደሮች የድርቅ ስጋት የለባቸውም፡፡ ከብቶች በጥጋብ ከመስክ ውለው ይገባሉ፤ ልማት አለ ውኃው አለ፤ መኖው አለ ቦረና ሁሉም ሙሉ ነው፡፡

 

ችግር ብልሃትን ይወልዳል እንዲሉ የቦረና ሕዝብ ለሌሎችም ጭምር ምሳሌ የሚሆን ሥራ ሠርቷል፡፡ ይህንን ተግባራዊ ላደረጉ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች እና ለቦረና ሕዝብ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገቢ ግብር አዋጁ ምን ይላል?
Next articleትምህርት ትውልድን ማስቀጠል በመኾኑ የትኛውም አካል በትምህርት ጉዳይ ዝም ሊል አይገባም።