
ባሕር ዳር: ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ከተለያዩ የክልል መሥሪያ ቤት መሪዎች፣ ከነዳጅ ባለ ማደያዎች እና ከጸጥታ ኀላፊዎች ጋር በነዳጅ ግብይት ዙሪያ በባሕር ዳር ከተማ እየመከረ ነው። በምክክሩ ላይ ነዳጅ የሁሉም ነገር መሠረት በመኾኑ ሕግ እና ሥርዓትን በተከተለ መንገድ ተደራሽ መኾን እንዳለበት ነው የተነሳው። የነዳጅ ግብይት እና ሥርጭትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አስደግፎ በመሥራት ሕገ ወጥነትን በዘላቂነት መከላከል እንደሚገባም ነው የተገለጸው።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን