መንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞው ታጣቂዎች በደብረ ብርሃን ከተማ የተሐድሶ ሥልጠና ጀመሩ።

14
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እስካሁን ከ72 ሺህ 500 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን በኮሚሽኑ የትሐድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብለዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መኾኑንም ገልጸዋል። በአማራ ክልል በሁለተኛው ዙር በሦሥት ማዕከላት ከ6 ሺህ በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሐድሶ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል። መንግሥት ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ እየሠራ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለተሐድሶ ሠልጣኞች አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የሰላምን አማራጭ ተቀብለው የመጡ የቀድሞ ታጣቂዎችም ክብር ይገባቸዋል ነው ያሉት። የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ሰላምን መምረጥ አስተዋይነትና ጀግንነት ነው ብለዋል። ጀግና እንደ ሀገር ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር የሚሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።
በመከላከያ ሠራዊት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አበባው ሰይድ የመከላከያ ሠራዊት በሕገ መንግሥቱ መሠርት ሕግ የማስከበር ኅላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል። የቀድሞ ታጣቂ የነበረው ሻንበል እንዳለው እስካሁን በጫካ ሆነን ሕዝባችንን በድለናል ብሏል። የነበርንበት የትጥቅ ትግል ሀገር እና ሕዝብን ለውጭ ጠላት አሳልፎ የሚሰጥ እና መጠቀሚያ የሚያደርግ ነበር ነው ያለው። እስካሁን ያጎሳቆልነውን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን ብሏል። በተሐድሶ ሥልጠናው ማስጀመሪያው ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊው አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) እና ሌሎችም የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለመተማ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። 
Next articleየተፈጠረውን ቁጭት ወደ ልማት መቀየር እንደሚገባ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) ገለጹ።