
15ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የኮሙዩኒኬሽን ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
አዲስ አበባ: ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 15ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የኮሙዩኒኬሽን ማኅበር ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ጉባዔው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት”ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ለአፍሪካ ትስስር” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።
በጉባኤ ላይ የተገኙት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ.ር) ሚዲያ ለአብሮነት፣ ለአንድነት እና ለጋራ ለስኬታማነት ሚናው የጎላ መኾኑን አመላክተዋል።
በኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ በጋራ መሥራት እና በጥምረት መጓዝን መምረጥ አዋጭ መኾኑን ነው የተናገሩት።
በጉባኤው ላይ የምሥራቅ አፍሪካ ኮሙዩኒኬሽን ማኅበር ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ማርጋሬት ጁኮ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ.ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ.ር)፣ ከአባል ሀገራቱ የተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎች እና አጋር አካላት እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፦ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን