
ጎንደር: ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተደራሽነቱን በማስፋት ዘመኑን የዋጁ አሠራሮችን በመከተል ለአድማጭ፣ ተመልካች እና አንባቢያን እየደረሰ ሦሥት አሥርት ዓመታትን አስቆጥሯል።
በእነዚህ ዓመታት የተለያዩ ፖለታካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎች በማዘጋጀት ወቅታዊ መረጃዎችን እያደረሰ ይገኛል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ተወካይ ኀላፊ አካሌ ፀጋዬ እንዳሉት አሚኮ በዘገባዎቹ የሥራ ዕድል ፈጠራው ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ አድርጓል።
አሚኮ የሥራ ዕድል ሊፈጠርባቸው የሚችሉ ፀጋዎችን በማመላከት እና የተፈጠሩ የሥራ ዕድሎችን ሞዴል እንተርፕራይዞች ለሌሎች ተሞክሮውን በማሣየት የበኩሉን ድርሻ መወጣቱን ተወካይ ኀላፊው አብራርተዋል።
በወጣቶች የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ በኩልም ድምጽ ኾኖ ማገልገሉ ተመላክቷል።
አሚኮ ዘመኑ ያፈራቸውን የቴክኖሎጅ አማራጮች በመጠቀም ለማኅበረሰብ ለውጥ እየተጋ መኾኑን በጎንደር ከተማ አሥተዳደር በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ የአንድ ማዕከል አሥተባባሪ አምሣሉ እያዩ ገልጸዋል።
አሥተባባሪው እንደገለጹት አሚኮ ከታች እስከ ላይ ያሉ አካላትን ግንዛቤ በመፍጠር የሥራ ዕድል ፈጠራው ውጤታማ እንዲኾን አድርጓል ብለዋል።
አሚኮ ለሥራ ፈጣሪዎች የብድር አቅርቦት እንዲመቻች ሲያግዝ መቆየቱንም ጠቅሰዋል።
በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ሥራ እና ሥልጠና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌታሠው ሙሉ በሥራ ዕድል ፈጠራው ማኅበረሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ እና መንግሥት የሚጠበቅበትን እንዲያሟላ የአሚኮ ድርሻ የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።
አሚኮ በቀጣይ በሥራ ዕድል ፈጠራው የሚገጥሙ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ መሥራት እንዳለበት የሥራ ኀላፊዎቹ አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ ማርታ አዱኛ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!