
ባሕርዳር: ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ የ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ ነው።
በዓሉን አስመልክተው የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኀላፊ ሀብታሙ እሸቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ሀብታሙ እሸቱ እንዳሉት አሚኮ ባለፉት ዓመታት የዞኑን ባሕል እና እሴት ከማስተዋወቅ ባሻገር የአካባቢውን ሰላም እና የማኅበረሰቡን አብሮ የመኖር ትርክት በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
ተቋሙ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ ባሕል፣ እሴት እና ቋንቋ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የብሔረሰቡ ሕዝብ “አሚኮ የኔ ነው” የሚል ስሜት እንዲኖረው አድርጓል ነው ያሉት።
ኀላፊው አሚኮ በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ድልድይ ኾኖ በማገልገል በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል።
በዚህም ከሰሜን ሸዋ እና አፋር አጎራባች ማኅበረሰብ ጋር ያለውን አንድነት እና ወንድማማችነት ለማጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
አቶ ሀብታሙ አሚኮ በቀጣይ በቁሳቁስ እና በሰው ኃይል ራሱን አጠናክሮ ወደ ሕዝቡ በመቅረብ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን በትኩረት እንዲሠራም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋ