
ሁመራ፡ ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመት በማስመልከት ከአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ስለተቋሙ ሃሳብ በመሠብሠብ ተከታታይ ዘገባዎችን ለአዳማጭ እና ተመልካቾች ሲያደርስ ቆይቷል።
አሚኮ ዛሬ ደግሞ ወደ ማይካድራ ከተማ አቅንቶ ከወሰን እና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባሉ አቶ ዳዊት ጥላሁን ጋር ቆይታ አድርጓል።
አቶ ዳዊት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በመርህ የሚሠራ እና ለሕዝብ ድምጽ የኾነ ሚዲያ ነው ብለዋል። የማይካድራ ከተማ ሕዝብ የደረሰበትን የጅምላ ጭፍጨፋ ለሕዝብ በማድረስ የአሚኮ አብርክቶ ከፍተኛ መኾኑንም ገልጸዋል።
“አሚኮ የሕዝብ ልሳን ነው” ያሉት አቶ ዳዊት ባለፈባቸው ዓመታት ራሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ የመጣ መኾኑንም አንስተዋል። አሚኮ ከኅብረተሰቡ የሚሰጡትን አስተያየቶች በመቀበል እና ራሱን በማዘመን ያደገ ተቋም ነውም ብለዋል።
አቶ ዳዊት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከለውጥ ማግስት የዞኑን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለሌላው ማኅበረሰብ በማድረስ ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረገ መኾኑንም አንስተዋል። በዚህም የሕዝቡ እና የተቋሙ ግንኙነት በየጊዜው እየጠነከረ መኾኑንም አንስተዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የወሰን እና ማንነት ትግል ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰው አሚኮ የሕዝቡን እውነት ፍትሕ ወዳድ ለኾነው ማኅበረሰብ የማሳወቅ ጥረቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አቶ ዳዊት ጠይቀዋል።
ለተሻ የኅብረተሰብ ለውጥ የአሚኮ እና የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አቶ ዳዊት አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ አምሳሉ አሞኘ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን