ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

297

ከቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት ንግድ ዝቅተኛ ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በያዝነው በጀት ዓመት ያለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶእንደነበር የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ አፈፃፀሙ ደግሞ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሆኑንየሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወንደሙ ፍላቴ ገልጸዋል፡፡ ይህም የዕቅዱን 79 ነጥብ 5 በመቶ ነው፡፡

አፈፃፀሙ በ2011 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 2 ነጥብ 15 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ271 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ብልጫ እንዳለውም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ጫት መሆናቸውንም የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ከዕቅድ አንጻር ከ50 በመቶ በታች ገቢ ያስመዘገቡ ዘርፎች ደግሞ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የቁም እንሰሳት ንግድ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

Previous articleየላፕቶፕ ባትሪ መልሶ አገልግሎት ላይ እንዲውል የሚያደረገው ፈጠራ ወደ ኢንዱስትሪ ደረጃ አልተሸጋገረም፡፡
Next articleየወይዘሮ ኬሪያ በፈቃዳቸው ኃላፊነት መልቀቅ ሕወሐት እየለዬለት፣ እየተሸነፈ መሄዱን እንደሚያሳይ ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ ተናገሩ፡፡