
ፍኖተ ሰላም: ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ጅጋ ከተማ አሥተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
በጉዳቱ የሰባቱ ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ቀሪዎቹ ሁለት ሰዎች ደግሞ ወደ ጤና ተቋም ገብተው ሕክምና ቢደረግላቸውም ማትረፍ አለመቻሉ ተገልጿል። ወቅቱ ክረምት በመኾኑ መሰል የትራፊክ አደጋዎች እንዳይከሰቱ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የጅጋ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ ኢንስፔክተር እንየው አበጀ አሳስበዋል ። በተለያዩ ጊዜያት የሚያገጥሙ የትራፊክ አደጋዎችን ለመከላከል ሁሉም በጋራ መሥራት አለበት ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!