ለሀገራዊ ምክክር ስኬት የሴቶች ሚና የላቀ ነው።

8
ደሴ: ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “የሴቶች ሚና እና አስተዋጽኦ ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በደሴ ከተማ አካሂዷል፡፡
የሴቶች ተሳትፎ ለምክክር ኮሚሽኑ ውጤታማነትም ኾነ ለሀገር ሰላም ግንባታ ወሳኝ ነው ያሉት የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀጣይ የሴቶች ተሳትፎ እንዲጎለብት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ገነት ስዩም የሀገራዊ ምክክሩ ተጨባጭ ውጤት እንዲያስመዘግብ በሚደረገው ሂደት ፌዴሬሽኑ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ስለመኾኑ ነው የገለጹት፡፡ ከደሴ ክላስተር የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሴት ተሳታፊዎችም ኮሚሽኑ ሁለንተናዊ እና አካታች እንዲኾን የሴቶች ተሳትፎ ከሪፖርት በዘለለ ውጤት በሚያመጣ መልኩ እንዲኾን መሠራት አለበት ብለዋል።
የሰላም እና የአንድነታችን ተስፋ የኾነው ኮሚሽኑ ምንም እንኳን በሰላም እጦት ምክንያት በፍጥነት አጀንዳ ለማሠባሠብ ቢቸገረም ምክክሩ እንዲፈጥን መሥራት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ለሀገራዊ መግባባት እና ጠንካራ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት መገንባት ከምክክር ኮሚሽኑ የሚጠበቅ ውጤት መኾኑን አንስተዋል፡፡ ሴቶችን ተሳታፊ ከማድረግ አኳያም 45 ነጥብ 5 በመቶ የሚኾኑት የኮሚሽኑ ተሳታፊዎች ሴቶች መኾናቸውንም አቶ መላኩ ወልደማርያም ተናግረዋል፡፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በቀጣይ ቀናትም ከሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ እንደሚያካሂድ ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ:- ፊኒክስ ሀየሎም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበእንስሳት እርባታ ተስፋ ሰጭ ውጤት ተገኝቷል።
Next articleየትምህርት መቋረጥ ትውልድን ለሥነ ምግባር ጉድለት ይዳርጋል።