አሚኮ ለጎንደር ባሕል ማዕከል ዕድገት የበኩሉን ሚና ተወጥቷል።

12
ጎንደር፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ ባለፉት 30 ዓመታት የባሕል እና ኪነ ጥበብ ዘርፎች እንዲጠበቁ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በትኩረት ሠርቷል።
አሚኮ የኪነ ጥበብ ዘርፉን የሚያሳድጉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የጎንደር ባሕል ማዕከል ሥራ አሥኪያጅ ወልደ አረጋይ ደሌ ተናግረዋል። የጎንደር ባሕል ማዕከል አሁን ለደረሰበት ደረጃ አሚኮ ዘገባዎች እና መሰናዶዎችን በመሥራት ለማዕከሉ ዕድገት የበኩሉን ሚና መወጣቱንም ጠቁመዋል። አሚኮ ታዋቂ የጥበብ ሰዎችን በማቅረብ ልምዳቸውን በማካፈል፣ ታዳጊ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተሠጥኦቸውን እንዲያውቁ እና ለሕዝብ እንዲተዋወቁ በርካታ ሥራዎችን እንደሠራም አብራርተዋል።
በተለይ በተቋሙ የሚተላለፈው የአርሶ አደሮች ወግ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የአርሶ አደሮችን ባሕል እንዲያውቁ እና በሥራቸው እንዲገልጹ ትምህርት የሚሰጥ መሰናዶ ነው ብለዋል። በባሕል ማዕከሉ የውዝዋዜ ባለሙያ የኾነችው ማሪቱ አዲሱ አሚኮ የጥበብ ከያኒያን ወደ ስኬት እንዲመጡ እና አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ የሚያስችሉ ዘገባዎችን መሥራቱንም ገልጻለች። አሚኮ ጥበብ እና ባሕል እንዲያድግ በተለይም የክልሉ ባሕል እና ኪነ ጥበብ ጎልቶ እንዲወጣ መሥራቱን ያነሳው ደግሞ በባሕል ማዕከሉ የመሰንቆ ተጫዎች ስጦታው ሙሉዓለም ነው። የጥበብ ሥራዎቹን አሚኮ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት የጎንደር ባሕል ማዕከል አባላት በቀጣይ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ውድድሮችን በማስጀመር ለጥበብ ዕድገት እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ :- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበ2017 በጀት ዓመት በመዲናዋ 19 ሺህ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋል።
Next articleአሚኮ በሚዲያ ኢንዱስትሪው የራሱን አሻራ ያበረከተ እና አንጋፋ ባለሙያዎችን ያፈራ ተቋም ነው።