አሚኮ በማኅበራዊ ዘርፍ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል፡፡

13
ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት የአሁኑ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) በታኅሣሥ 7/19 87 ዓ.ም በበኩር ጋዜጣ አስተማሪ እና አዝናኝ የኾኑ መረጃዎችን ለኀብረተሰቡ በማድረስ ጀምሯል፡፡
በሂደትም በቴሌቪዥን፣ በመደበኛው ሬዲዮ፣ በኤፍ ኤም፣ በብሔረሰብ ጋዜጦች እና በዲጂታል ሚዲያ አማካኝነት አድማሱን በማስፋት እነሆ 30 ዓመታትን ደፍኗል፡፡ የአሚኮ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መሠረት አስማረ እንደሚሉት ተቋሙ የማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ሥራዎችን መሥራት ግዴታየ ነው ብሎ ያምናል ይላሉ፡፡ አሚኮ የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎችን ከሚሠራባቸው መንገዶች መካከልም አንዱ የይዘት ሥራ ነው፡፡ በዚህም ተቋሙ ባለፉት ዓመታት ባሉት ሚዲየሞች በርካታ የተለያዩ ይዘት ያላቸው የማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎችን ሠርቷል ብለዋል፡፡ እንደ አብነት ብንወስድ ፕሮግራም እንዲሠራላቸው የሚፈልጉ ግን ደግሞ አቅም የሌላቸው ተቋማት ይዘታቸው ቢሠራ እና አየር ላይ ቢውል ለክልሉም ኾነ ለሀገር ጠቃሚ ነው ብሎ ያመነበትን ተግባር በዘገባው ሽፋን ሰጥቷል ነው ያሉት፡፡
አቅም የሌላቸው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ማሠራት የሚፈልጉ ግለሰቦችንም በነጻ በማስተናገድ በኩል የሠራው ሥራም ቀላል አይደለም ነው ያሉት፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ በማስታወቂያ እና በተለያዩ የይዘት ዘገባዎቹ እስከ 8 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የተለያዩ የማኅበራዊ አገልግሎት ሥራዎችን ሠርቷል ነው ያሉ፡፡ አሚኮ የአሚኮ ቤተሰብንም ኾነ ከአሚኮ ውጭ ያሉ አቅም ያነሳቸው አካላትን በሙሉ ችግራቸውን በማየት በዓይነትም ድጋፎችን ሲያደርስ ቆይቷል ነው ያሉት፡፡ ዳይሬክተሩ ከዚህ ውጭ በዕቅድ አካትቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ የተሟላ የትምህርት ግብዓት እና የመማሪያ ክፍል ምቹ የማድረግ ሥራ እንዲሠራ ማኅበረሰቡን በማነሳሳት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በማድረክ በኩል አሚኮ የሠራቸው ሥራዎችም ቀላል የሚባሉ አይደሉም ነው ያሉ፡፡
በየበዓላቱ አቅም ለሌላቸው የአካባቢው ማኅበረሰብም የበዓል መዋያ የተለያዩ የምግብ ግብዓቶችን ድጋፍ ስለማድረጉም ጠቁመዋል፡፡
ከሠራቸው ማኅበራዊ ድጋፎች ውስጥ የአረጋውያን ቤትን የማደስ ሥራም አንዱ ነው ብለዋል፡፡ በጦርነት እና በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎችም የምግብ እና የአልባሳት ድጋፎችን በማድረግ በኩል ትልቅ ሥራ ስለመሠራቱም ነው ያስገነዘቡት፡፡ የአረጋውያን ማኅበራትን እንደነ ሜቄዶንያ፣ ዝግባ፣ የሕዝብ አንባ እና ሌሎችን ማኅበራዊ ተቋማት በቋሚነት እንደሚደግፉም ነው የተናገሩት፡፡ የአሚኮ ሠራተኞችን በማስተባበርም በቋሚነት ድጋፍ በማድረግ ትምህርታቸውን እንዲማሩ የተመቻቸላቸው ተማሪዎች እንደነበሩም አስታወስዋል፡፡ በዚህም ተማሪዎችን አስመርቆ እራሳቸውን በማስቻል በኩል የተሠራው ሥራ ተቋሙን የሚያስመሠግን ስለመኾኑም ጠቁመዋል፡፡ በቀጣይ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በመመልመል ግብዓቶችን በማሟላት በቋሚነት ለማገዝ ሥራ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችን ለማገዝም በዝግጅት ላይ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሰናይት በየነ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article” ከራሳችን አልፎ አፍሪካን በባቡር ለማስተሳሰር በአዲስ ምዕራፍ በጋራ መሥራት ይጠበቅብናል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleእኛስ ያጣነውን ሰላም ለመመለስ ስንት ዓመታትን እናልቅስ?