የአሸንድዬ በዓል በላሊበላ እየተከበረ ነው።

21
ባሕርዳር፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸንድዬ በዓል ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው የልጃገረዶች በዓል ነው።
የአሸንድዬ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የታሪክ መነሻነት የሚከበር በዓል ነው። ቀዳሚው በኦሪት ዘፍጥረት ላይ የሚገኘ የመዳን፣ የደስታ፣ የነጻ መውጣት ምሳሌ ነው። ይሄውም እርግቧ የለመለመ ቅጠል በማምጣት የውኃ ሙላቱ መጉደሉን በመግለጿ ኖህ ከነልጆቹ እግዚአብሔርን አመስግኗል። ዛሬም ልጃገረዶች የደስታ፣ የመዳን እና የነጻነት ምሳሌ የሆነውን የአሸንድዬን ቅጠል ይዘው ይጫወታሉ።
ቅድስት ድንግል ማርያምን መላእክት በክንፋቸው እያሸበሸቡ አሳርገዋታል። የአሸንድዬ ተጨዋቾችም ይሄን አብነት በማድረግ እንደ መላእክት ክንፍ ከወገባቸው አሸንድዬን አስረው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያመሰግኑበታል። ከላሊበላ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው አሸንድዬ በላሊበላ በድምቀት እየተከበረ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሶለል በራያ እየተከበረ ነው።
Next article“ፈተናዎች ያልበገሩት፣ ችግሮች ያልገቱት”