
ባሕርዳር፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሶለል የልጃገረዶች የነፃነት በዓል ነው። ከነሐሴ 16 ጀምሮ የሚከበረው የሶለል በዓል በናፍቆት ይጠበቃል። ከቆቦ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሶለል በሰሜን ወሎ ዞን ከራያ ባላ ፣ከራያ አላማጣ፣ ከአላማጣ ከተማ ፣ከራያ ቆቦ እና ከቆቦ ከተማ የተውጣጡ የሶለል ተጨዋች ልጃገረዶች በተገኙበት በቆቦ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። ሶለል የራያ መገለጫ እና ተናፋቂ በዓል ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!