
ሰቆጣ፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሻደይ በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በሰቆጣ ከተማ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ በርናባስ ሻደይ የሰላም እና የፍቅር ምልክት ነው ብለዋል። በኖኅ ዘመን የነበረው የውኃ ሙላት መጉደሉን ለማብሰር እርግብ የሰላም ቄጤማ እንዳመጣች ሁሉ ዛሬም ደናግል ዘማርያን የሻደይ ቄጤማ ይዘው እየዘመሩ ይውላሉ ነው ያሉት። በኖኅ ዘመን ቄጤማ ሰላምን፣ ደስታን፣ ፍቅርን እንዳበሰረ ሁሉ ዛሬም የሻደይ ቄጤማ የምህረት የደስታ፣ የሰላም ተምሳሌት ኾኖ በቤተክርስትያኗ እየተከበረ መምጣቱን አንስተዋል። ዛሬም ሀገራችን ሰላም እና ፍቅር ያስፈልጋታል ያሉት ብፁዕነታቸው በዓሉን ስናከብር ለሀገር ሰላም በመስበክ እና በመተባበር ሊኾን ይገባል ብለዋል። የተቸገሩትን ወገኖች በመርዳትና በመደገፍ በዓሉን ማክበር እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዘጋቢ ፦ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!