
ሰቆጣ፡ ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው የሻደይ በዓል በሰቆጣ ከተማ ደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በብፁዕ አቡነ በርናባስ አባታዊ ቡራኬ ነው መከበር የጀመረው። የሻደይ በዓል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት በሚዘክሩ መንፈሳዊ ወረቦች እና መዝሙሮች ነው እየተከበረ የሚገኘው።በበዓሉም ሴት ደናግላን የሻደይን ቅጠል አስረው ወረብ እያቀረቡ ይገኛሉ። በበዓሉበ ሊቃውንት፣ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከፍተኛ መሪዎች፣ የሰቆጣ ከተማ የሥራ ኀላፊዎች፣ ምዕምናን እና የየወረዳ የሻደይ ተጫዋቾች በበዓሉ እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ ፦ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን