
ጎንደር: ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን 30ኛ ዓመቱን በተለያዩ ኹነቶች እያከበረ ይገኛል።
የጎንደር ኤፍ ኤም 105 ነጥብ 1 ሬዲዮ ጣቢያ ባለሙያዎችም የአሚኮን 30ኛ ዓመት አስመልክቶ በተቋሙ ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል። የጎንደር ኤፍ ኤም 105 ነጥብ 1 ሬዲዮ ጣቢያ ኀላፊ ጋዜጠኛ እመቤት ሁነኛው ሚዲያ የተለያዩ ጉዳዮችን መዘገብ ብቻ ሳይኾን በልማት ሥራዎችም መሳተፍ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የአሚኮን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በጣቢያው ሁሉም ባለሙያዎች የተሣተፉበት ለውበት እና ምጣኔ ሃብታዊ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል። የተተከሉ ችግኞች የግቢውን ውበት በመጠበቅ ለዘገባ ምቹ እንዲኾኑ የመንከባከቡን ሥራ በትኩረት እናከናውናለን ብለዋል። የተቋሙን 30ኛ ዓመት በችግኝ ተከላ፣ በደም ልገሳ፣ በስፖርታዊ ውድድር እና በተለያዩ ሁነቶች የጎንደር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ እንደሚያከብርም ኀላፊዋ አመላክተዋል።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!