
ደሴ: ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን ልማት ቡድን መሪ ማማየ ደምሴ በዞኑ 20 ወረዳዎች ከ23 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በአንድ ቀን ለማስመዝገብ ታቅዶ ተሠርቷል ብለዋል።
ይህ የሙከራ ምዝገባ መርሐ ግብር ከነሐሴ 19/2017 ጀምሮ ለሚካሄደው የምዝገባ ፕሮግራም ተሞክሮ የሚቀመርበት መርሐ ግብር መኾኑን አስረድተዋል። ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆችም ለመጪው የትምህርት ዘመን መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት። ነገር ግን በደጋን ከተማ በተለምዶ ቻይና ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ለልጆቻቸው የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት እንደተቸገሩ ተናግረዋል። የቃሉ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እንድሪስ አራጋው በወረዳው በ106 ትምህርት ቤቶች ከ64 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን ገልጸዋል።
የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የሚደረግላቸው እንዳሉ የተናገሩት አቶ እንድሪስ ከ14 ሺህ በላይ ደርዘን ደብተር ለማሰባሰብ እየተሠራ ነው ብለዋል።
እስካሁን ከ1 ሺህ 500 በላይ ደርዘን ደብተር ተሰባስቧል፤ ለተፈናቃዮችም 100 ደርዘን ደብተር ድጋፍ ይደረጋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ከድር አሊ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
