የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

23
ትውልድ እና ዘመን ተሻጋሪ ሥልጣኔን ለምታውቀው ሐረር ዐረንጓዴ አሻራ ሌላው መለያ ቀለሟ ነው። በመትከል የማንሰራራት አረንጓዴ አሻራችንን ዛሬ በሐረር ድሬ ጠያራ ወረዳ አሳርፈናል። የታሪክ እሴቷን ጠብቃ የቱሪዝም እና በአጠቃላይም በተነቃቃ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የምትገኘውን ሐረርን አረንጓዴ ማልበስ የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ሐረርን የታሪክ እና የቅርስ ከተማ ብቻ ሳይሆን የአረንጓዴ ልማት ማሳያ ሙዚዬም ልናደርጋት ይገባል። በዘንድሮው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በሁሉም አካባቢ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞችን ተክለናል። ሁላችንም በአንድ እጃችን እየተከልን በአንድ እጃችን ደግሞ መንከባከብ ይገባናል።
Previous articleበአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል።
Next articleየጸረ ተባይ እና ጸረ አረም ኬሚካል እጥረቶች እንዳሉባቸው አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡