በኢትዮጵያ 136 ተጨማሪ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፡፡

176

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/2012 ዓ.ም (አብመድ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 775 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ136 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 156 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባው ሰዎች ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 97 ዓመት ነው፡፡ ዛሬ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው መካከል 12 ሰዎች የውጭ ዜጎች ናቸው፤ 115 ሰዎች ደግሞ ከአዲስ አበባ ናቸው፤ ቀሪዎቹ ከተለያዩ ክልሎች (ኦሮሚያ (9)፣ ትግራይ (7)፣ ሐረሪ (2)፣ ሶማሌ (2) እና ደቡብ ብሔሮች ብሔሰረቦችና ሕዝቦች (1)) ናቸው፡፡

ትናንት ከአዲስ አበባ (8)፣ ከአማራ ክልል (5)፣ ከአፋር ክልል (2) እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል (2) በድምሩ 17 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 361 ደርሷል፡፡

ኢትዮጵያ እስከዛሬ ለ147 ሺህ 735 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ አድርጋለች፤ በዚህም በ2 ሺህ 156 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን አረጋግጣለች፡፡ በቫይረሱ ተይዘው 27 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ 32 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ሕሙማን የሕክምና መከታተያ ክፍል ይገኛሉ፡፡ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በሕክምና ክትትል ላይ የሚገኙት ደግሞ 1 ሺህ 766 ናቸው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየሀገሪቱ የወጭ ንግድ 13 በመቶ ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታወቁ፡፡
Next articleበኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡