
ጎንደር: ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ነዋሪው ጋሻው አስማረ አሚኮ በአማራ ክልል የሚገኙ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በማስተዋወቅ በኩል ከፍ ያለ ድርሻ ወስዷል ብለዋል።
አሚኮ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በመሥራቱ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኝዎች ቅርሶችን እንዲጎበኙ ዕድል ፈጥሯል ነው ያሉት።
አማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን ለአማራ ሕዝብ ብሎም ለኢትዮዽያውያን አዳዲስ መረጃዎችን በትኩሱ እና ግልጽ በኾነ መንገድ ለሕዝቡ ተደራሽ እንዲኾን አድርጓል ያሉት ደግሞ ሌላው የጎንደር ከተማ ነዋሪ ማርቆስ አንዳርጌ ናቸው።
አሚኮ ቦታ ሳይገድበው ከገጠር እስከ ከተማ ተደራሽ መኾን ችሏል ያሉት አቶ አበበ ገብረ ሥላሴ የግብርና ሥራ እንዲሻሻል ምርት እና ምርታማነት እንዲያድግም የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል።
አሚኮ አሁን ከሚሠራው ሥራ በላይ እንዲሠራ እንጠብቃለን ያሉት ነዋሪዎቹ ሰላም እንዲሰፍን ከሕዝቡ ጋር ኾኖ መሥራት አለበት ሲሉም አመላክተዋል።
አሚኮ ትውልዱ ሀገሩን፣ ባሕሉን እና ወጉን የሚወድ እንዲኹም የሚጠብቅ እንዲኾን ማስተማር አለበትም ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ተስፋዬ ጋሹ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!