የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት፦

36

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት፦

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በቀደመ የታሪክ ጌጥ እና በዛሬ ፈጣን ልማት እየደመቀች ወዳለችው የሰላም ከተማ እና የሕዝቦች ኅብረት ሞዛይክ ወደ ሆነችው የሐረር ከተማ ገብተናል፡፡

የሐረር ከተማ ትናንትን ባከበረ የዛሬ ልማት፣ ታሪክን እሴት ባደረገ የከተማ እና የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ትገኛልች፡፡
ወደ ከተማዋ ስንገባ የደመቀ እና የሀረርን እንግዳ ተቀባይነት በሚያስመሰክር መልኩ አቀባበል ላደረጉልን ለክልሉ ፕሬዝዳንት እና ካቢኒያቸው፣ ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ሕዝብ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

በሐረር ከተማ በሚኖረን ቆይታም የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጨምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሥራ ሂደት የምንመለከት ይኾናል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና በባሕር ዳር ከተማ ተጀመረ፡፡
Next articleየማኅበረሰቡን እሴት አደጋ ላይ የሚጥሉ የቁማር ተግባራትን ማስቆም ይገባል።