
ምክክርን ወደ ባሕል በመቀየር ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ይቻላል።
ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የምሁራን ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል ርእሰ ጉዳይ በባሕር ዳር ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ.ር) በምክክሩ የምሁራን ተሳትፎ ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ነው ያሉት።
የምሁራን ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ጊዜው ችግር በምክክር የሚፈታበት ነው ብለዋል።
በዓለም ላይ የሚገኙት ኃያላን መንግሥታትም ልዩነታቸውን በምክክር እየፈቱ ስለመኾናቸው ያነሱት ኮሚሽነሩ ምክክርን ወደ ባሕል መቀየር ሲቻል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።
ምክክር ተከታታይነት ሲኖረው እና ሁሉም ተሳታፊ ሲኾን ደግሞ ፍሬያማ ይኾናል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation