አሚኮ ለሀገር ሰላም እየሠራ ነው።

15
ገንዳ ውኃ: ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው።
የአሚኮን 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አስመልክተው ሀሳባቸውን የሰጡን በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቃሲም አብዴ ሚዲያው ተደራሽነቱን በማስፋት አዲስ ነገሮችን ለሕዝቡ እያሳወቀ ነው ብለዋል። አሚኮ የትምህርት ጥራት እንዲመጣ ባለድርሻ አካላትን በማነጋገር የግብዓት ችግሮች እንዲሟሉ እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመጡ ተደጋጋሚ ሥራ በመሥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
አካባቢው በረሃ በመኾኑ የሚከሰቱ ወረርሽኞች ጉዳት እንዳያደርሱ ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጤናው ዘርፍም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። በቀጣይ ይህን ተግባሩን እና የሚዲያ ተደራሽነቱን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል። አሚኮ በክልሉ ዕድገት ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥር እና ለሀገሪቱ ዕድገት የሚሠራ ተቋም መኾኑን የገንዳውኃ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕጸት ቤት ኀላፊ ገብረ ኪዳን መንጋው ገልጸዋል። የአካባቢውን ባሕል፣ እሴት እና ፀጋዎችን የማስተዋወቅ ሥራዎችን ሠርቷል ነው ያሉት።
በግብርናው ዘርፍም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው የተናገሩት። አሚኮ ሀገር እንድትበለጽግ እና ሰላም እንድትኾን እየታተረ ያለ ተቋም መኾኑንም ተናግረዋል። ዞኑ ላይ የራዲዮ ጣቢያ ለመክፈት የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ በመቀጠል የኢትዮ-ሱዳን ግንኙነቱን ማጠናከር ይገባዋል ነው ያሉት። የመተማ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ኤደን ምንውየለት የአማራ ሕዝብ ድምጽ ኾኖ ሥራውን የጀመረው አሚኮ ሀገር አቀፍ ይዘቱን አስጠብቆ እና አድማሱን በማስፋት ለሀገር ብልጽግና እየሠራ ነው ብለዋል። ሰላም እንዲሰፍን ሢሠራ መቆየቱንም አንስተዋል። የሴቶችን መብት በማስጠበቅ፣ የሕግ ከለላ እንዲያገኙ፣ ከጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲወጡ በማድረግ እና በኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲኾኑ ሚዲያው አበርክቶው የላቀ መኾኑን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ስሙን የወረስሽ፣ ክብሩን የጠበቅሽ”
Next articleየአርቲስት ደበበ እሸቱ አስክሬን ሽኝት መርሐ ግብር በብሔራዊ ቴአትር እየተካሄደ ነው።