
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የኮሮናቫይረስ በጤና፣ በቱሪዝም እና በኢኮኖሚው ላይ እያሳደረ ስላለው አሉታዊ ተፅዕኖ ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
• የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ከ213 በላይ ሀገራትን ያጠቃ፣ ከ100 ዓመታት በኋላ አስፈሪ ክስተት መሆኑን በመግለጽ በዓለም ላይ7 ሚሊዮን ሰዎችን እንደያዘ፣ ከ400 ሺህ ያላነሱ ሰዎችን ሕይወት እንደነጠቀ፣ በንጽጽር ቁጥሩ ያነሰ የሚመስል ግን በፍጥነት እያደገ ያለ ጉዳት በአፍሪካም እያደረሰ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በአህጉሩ5 ሺህ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉንም ጠቅሰዋል፡፡
• ከአፍሪካ በምሥራቁ ክፍል አነስተኛ ቢመስልም 18 ሺህ በቫይረሱ ተይዘው ከ580 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ቁጥሩ ያነሰ ቢመስልም ሕይወት የመቅጠፍና የመስፋፋት አቅሙ እያደገ መሆኑን፣ በኢትዮጵም2 ሺህ 20 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው27 ሰዎች ሕይወታቸውንማጣታቸውን አብራርተዋል፡፡
· ከዓለምና ከአፍሪካ የመግደል አቅም አንጻር እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘው ሰውና የሞተው ቁጥር አነስተኛ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም ኮሮናን የመናቅና የመዘናጋት ዝንባሌ ይታያል፤ በኢትዮጵያ ዘጠኙም ክልሎችና ሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተውባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወረርሽኙ ብዙ ቤተሰብ በትኗል፤ በርካታ ቤተሰብ ለሐዘን ዳርጓል የኑሮ ዘየን ፈትኗል፤ ኢኮኖሚን በዓለም ደረጃ አንኮታኩቷል በማለት የቫይረሱን አስከፊነት አስረድተዋል፡፡ ኮሮናቫይረስ 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ዓለምን የፈተነ አደገኛ በሽታ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
· ወረርሽኙ በኢኮኖሚው የአቅርቦትና ፍላጎት መውረድ አዙሪት መፍጠሩን የገለጹት ዶክተር ዐብይ ምርት በገበያ የመገኘት ዕድል እንዳይኖረው፣ ምርቶችም ገበያ እንዳያገኙ አድርጓል፡፡ ይህም አዙሪት የነበረውን ፍላጎት እንደገና በመፍጠር ማቅናትን የሚጠይቅ ሆኗል፤ ይህንን በአጭር ጊዜ ለመመለስ ደግሞ ፈታኝ ሆኗል ብለዋል፡፡
· በጤና ዘርፍ ያለውን ወረርሽ ለመመከት ሲሠራ ኢኮኖሚውንም ወረርሽኙ እንደሚፈትነው በማስረዳትም ኢኮኖሚ በራሱ ዑደት ሲፈተንና በውጫዊ ተጽእኖ ሲፈተን መፍትሔው ተመሳሳይ አለመሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
· የዓለም የገንዘብ ተቋም በዚህ ዓመት170 ሀገራት ከዜሮ በታች እድነገት እንደሚኖራቸው ማሳወቁት በማንሳትም የዓለም ምጣኔ ሀብት በ9 በመቶ እንደሚወርድ እንደሚጠበቅ፣ ይህ ግን በሁሉም ሀገር እኩል ተጽዕኖ እንደማይኖረው አብራርተዋል፤ ለዚህ የሚመጥን ስትራቴጅ እንደሚያስፈልግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
· ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለምክር ቤት አባላት እንደገለጹት የዓለም የሸቀጥ ፍላጎት በ27 በመቶ ወርዷል፤ በዓለም 350 ሚሊዮን ሰዎች ከሥራ ገበታ ተፈናቅለዋል፡፡ ከ100 እስከ200 ሺህ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንኳ ከሥራ ተፈናቅለው ከሆነ ሀገርም ቤተሰብም ለችግር ተጋልጠናል ማለት ነው፡፡
· በሌላ በኩል ደግሞ የዓለም ምግብ ድርጅትም265 ሚሊዮን ሕዝብ ለርሀብ እንደሚጋለጥ ማስታወቁን በመግለጽ ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው እጥፍ መሆኑን፣ ችግሩ በኢትዮጵያም አስጊ መሆኑን አመላካች እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
· ዶክተር ዐብይ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ የቱሪስት መዳረሻዎች 80 ከመቶ ለኪሳራ እንደተዳረጉ፣በተለይየአፍሪካ ክፉኛ መጎዳቱንና የኢትዮጵያም የቱሪስት ዕድገት ከነበረው አቅሙ እንደተዳከመ ነው ያስረዱት፡፡
· የኮሮናቫይረስ ታላላቅ አየር መንገዶች በመጋቢት ብቻ 28 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ ውስጥ እንዲገቡ ማድረጉን ያበራሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ፣ በማኅበራዊ ዘርፍም ከፍተኛ ጥፋት ማስከተሉን ገልጸዋል፡፡ ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉም ስፓኒሽ ፍሉ ሲነሳ1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ሕዝብ ነበር፤ ዘንድሮ ግን1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ከትምህርት ገበታ የተፈናቀሉ ተማሪዎች ቁጥር ነው፡፡ ትምህርት ከብዙ ጥፋት ይታደጋል፤ አሁን ከትምህርት ሲርቁ ብዙ ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡60 ሚሊዮን ሕዝብም ለድኅነት ተጋልጧል ብለዋል፡፡
· ከወረርሽኙ በኋላ በትምህርት ሥርዓት፣ በአኗኗር፣ በፖለቲካዊ ሁኔታ አዲስ ልምምድ የሚጠይቅ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮሮናቫይረስ ከ50 ያላነሱ ሀገራት ምርጫ እንዲያራዝሙ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡