የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ አደረጃጀቶች ከተውጣጡ ሴቶች ጋር እየመከረ ነው።

18
ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “የሴቶች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው።ውይይቱ ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ እንደኾነ ተገልጿል። በውይይት መድረኩ ከተለያዩ ተቋማት፣ ሲቪክ ማኅበራት እና አደረጃጀቶች የተወከሉ ሴቶች ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት። በመድረኩ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህንን ጨምሮ ሌሎችም የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦
Next articleየነገ የሀገሪቱ መልክ የሚወሰነው በዛሬ ተማሪዎች ነው።