ዓለም ተስፋ የጣለበት የሁለቱ መሪዎች ውይይት ያለበቂ ስምምነት ተቋጨ።

39
ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው ዓለም ውጤቱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአላስካው ውይይት ያለበቂ ስምምነት ተቋጭቷል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው ቪላድሚር ፑቲን በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በሩሲያ-ዩክሬን ግጭት ዘላቂ መፍተሄ ዙሪያ በአላስካ ተገናኝተው መክረዋል። ሦስት ሰዓታትን ከፈጀው ውይይት በኋላ መሪዎቹ የጋራ መግለጫም ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በተለይ በሩሲያ-ዩክሬን የሰላም ጉዳይ ላይ በተደረገው ውይይቱ ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ አለመደረሱን ጠቅሰው ነገር ግን የተሻሻለ እና ተስፋ ሰጪ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በበኩላቸው ከዩክሬን ጋር የገቡበትን ግጭት ለማስቆም “ከልብ ፍላጎት አለኝ” ቢሉም ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን መስጠት ግን አልፈለጉም። ምናልባትም ሁለቱ መሪዎቹ ዳግም በሞስኮ ሊገናኙ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን በመግለጫቸው ጠቆም አድርገዋል። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ሁለቱ መሪዎች በጋራ ከሰጡት መግለጫ ውጪ የጋዜጠኞችን ጥያቄ ከማስተናገድም ተቆጥበዋል።
በታዘብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየሁለቱ ኃያላን ሀገራት መሪዎች ፊት ለፊት ተገናኙ።
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦