
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሲ ኤን ኤን በቀጥታ ባስተላለፈው ስርጭት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቫላድሜር ፑቲን ጋር በአላስካ ተገናኝተዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ በንግግሩ ላይ ግልጽ የኾነ የድርድር ሀሳብ ይዛ እንደምትቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌይ ላቭሮቭ ቀድመው አስታውቀው ነበር። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ቀድመው በሰጡት መግለጫ፤ ሀገራቸው ሩሲያ አሜሪካ በቀላሉ የምትረዳውን ግልጽ የድርድር ሃሳብ ይዛ ትቀርባለች ብለዋል፡፡ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍም ውይይቱ ሁለቱንም ወገኖች አሸናፊ የሚያደርግ አንድምታ እንዳለው ገልጸዋል። አሁን ላይ ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ፊት ለፊት የተገናኙ ሲኾን የተገናኙበት ውይይት መቋጫ አጓጊ ኾኗል።
በአሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!