
ባሕር ዳር: ነሐሴ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከሦስት ዓመት በላይ ያስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት መፍትሔ ሳያገኝ ዛሬ ላይ ደርሷል።
ጦርነቱ መቋጫ ያገኝ ዘንድ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በአላስካ ለመምከር ዛሬ ከቆይታ በኋላ ፊት ለፊት ይገናኛሉ። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከዋሽንግተን ተነስተዋል። እስከ ሰባት ሰዓት የሚደርስ የአውሮፕላን ጉዞ አድርገው በአላስካ ውይይቱን ይጀምራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ትራምፕ የዚህን የውይይት መድረክ ትልቅነት እና ክብደት በትሩዝ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ሲገልጹ “ከፍተኛ ዕድሎችም ሥጋቶችም ያሉት ጉዳይ ነው” ብለውታል።
ትራምኘ አውሮፕላን ውስጥ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ የጉዟቸው ዓላማ በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ማደራደር ሳይኾን ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ ለመመካከር እንደኾነ ሲ.ኤን.ኤን አስነብቧል። በሁለቱ ፕሬዝዳንቶች መካከል የሚደረገው ውይይት የሰባት ሰዓታት ቆይታ ሊኖረው እንደሚችል የዘገበው ደግሞ ቢቢሲ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
