
ደብረ ማርቆስ፡ ነሐሴ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ ብርቄ ይዘንጋው አሚኮ በባሕል እና ቱሪዝም ዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ ትልቅ ተቋም ስለመኾኑ ተናግረዋል፡፡
አሚኮ በዞኑ የሚገኙ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ቅርሶችን ለማስተዋወቅ የሄደበት ርቀት የሚያሥመሠግን ነው ብለዋል፡፡በዞኑ የሚገኙ ታሪካዊ ገዳማት እና ሃይማኖታዊ በዓላት እንዲተዋወቁ ብሎም እንዲጎበኙ ተቋሙ የማይተካ ሚና መጫወቱን መምሪያ ኀላፊዋ ተናግረዋል፡፡
አሚኮ ችግር ሳይበግረው የኅብረተሰቡን ባሕል፣ ወግ እና ጠቃሚ እሴቶች በመዘከር በተለያዩ ሚዲየሞቹ ለሕዝብ በማድረስ ኀፊነቱን በአግባቡ የተወጣ ተቋም ስለመኾኑም አብራርተዋል፡፡አሚኮ የአማራን ሕዝብ ባሕል፣ ወግ እና ታሪክ ለዓለም ለማስተዋወቅ እየሠራ ያለው ሥራ የሚበረታታ ነው ብለዋል።ኀላፊዋ በአጠቃላይ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች አንደ ክልል ብቻም ሳይኾን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተቋሙ እየተጫወተ ያለውን ሚና ማስቀጠል ይገባል ነው ያሉት፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!