የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከወጣቶች ጋር በባሕር ዳር እየመከረ ነው።

17
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “የወጣቶች ሚና እና ተሳትፎ ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ውይይት እያካሄደ ነው።
ውይይቱ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ እንደኾነ ተገልጿል። በውይይት መድረኩ ከሲቪክ ማኅበራት፣ ተቋማት እና አደረጃጀቶች ከተወከሉ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች እየተሳተፉ ነው። የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ብሌን ገብረመድህንን ጨምሮ ሌሎችም የሥራ ኀላፊዎች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ከዕድሜው ያለፈ፤ በብርታቱ የገዘፈ”
Next articleምክንያቱ ያልታወቀ የአንጀት ቁስለት ምንድን ነው?