አሚኮ ወንድማማችነት እንዲጎለብት አድርጓል።

5
ከሚሴ: ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል።
የምሥረታ በዓሉን በማስመልከት በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም የአማራ ክልል ከነበረበት የሰላም እጦት እንዲወጣ እና “አሁን ያለው አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ የአሚኮ ሚና የላቀ ነበር” ብለዋል።
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሚሠሩ የሰላም ግንባታ ተግባራትን አሚኮ በወረዳዎች እና በቀበሌዎች በመገኘት እና የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማናገር እውነታውን ለሕዝቡ እያደረሰ የድርሻውን በሚገባ መወጣቱንም ተናግረዋል። በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሚደረጉ ሕዝባዊ ውይይቶችን በቦታው በመገኘት ለሕዝብ እንዲደርስ የሠራ ተቋም ነውም ብለዋል። በተለይ ከአፋር እና ከሰሜን ሸዋ ዞን ጋር ያለው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚካሄዱ የጋራ የሰላም መድረኮችን ተከታትሎ በመዘገብ በቀጣናው ወንድማማችነት እንዲጎለብት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሕዝብ በቋንቋው ሀሳቡን እንዲያንጸባርቅ ማድረጉን እና ባሕሉን እና እሴቱን እንዲያስተዋውቅ የሠራው ተግባር አሚኮን የሚያስመሰግን መኾኑንም አስረድተዋል። በቀጣይም በብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሚሠሩ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ለኅብረተሰቡ በጥራት እና በፍጥነት ማድረሱን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም ብለዋል።
ዘጋቢ: ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበደሴ ከተማ አሥተዳደር የፖሊስን ሥራ ለማዘመን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች አበረታች ናቸው።
Next articleከነገ ጀምሮ ምርጫ እንደሚያካሂድ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ።