አሚኮ ሰላም እና አብሮነት እንዲጎለብት ከፍተኛ ድርሻ እየተወጣ ነው።

14
ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከዛሬ 30 ዓመት በፊት በውስን ሃብት እና የሰው ኃይል ሥራ የጀመረው አማራ ማዲያ ኮርፖሬሽን የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል። የአሚኮን የምሥረታ በዓል በማስመልከት የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤሊያስ አበበ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም እጦት ወደ ነበረበት ለመመለስ በተከናወነው ሥራ ላይ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ብለዋል። በክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር በውይይት እንዲፈታ ለማድረግ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና የሀገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር አሚኮ የሠራው ዘገባ በአርዓያነት የሚነሳ እንደኾነ ነው የገለጹት። በየደረጃው የተካሄዱ ሕዝባዊ ውይይቶች እና ሀገራዊ ምክክሮች የዚህ ማሳያ መኾናቸውንም ጠቅሰዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አጎራባች ወረዳዎች ላይ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲጎለብት እና ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር አሚኮ ከፍተኛ ድርሻ መወጣቱንም ተናግረዋል።የሰሜን ሸዋ ዞን ልማት ቀጣይነት እንዲኖረው የሚዲያው አበርክቶ የላቀ ነበር ያሉት ኀላፊው የሕዝቡ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እየሠራ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት። አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሕዝብን ሰላም እና አብሮነት የሚያጠናክሩ ሃሳቦችን እየተገበረ እንደኾነ ነው የገለጹት።
ዘጋቢ: ሀብታሙ ዳኛቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ላይ አስገዳጅ ሕጎች እንዲወጡ እየተሠራ ነው።
Next articleሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ግብርና በአፍሪካ።