
አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አሥፈፃሚ ቦርድ በሰጠው መግለጫ የምርጫ የቅድመ ዝግጅት ምዕራፉን በማጠናቀቅ ወደ ምርጫ ምዕራፍ መሸጋገሩን አስታውቋል።
ምርጫ የሚከናወንባቸው ቀናትንም ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አሥፈፃሚ ቦርድ አባል ጣሀር ውሃበረቢ እንደገለጹት ከሐምሌ 30/2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 4/2017 ዓ.ም የሹራ ቀናት ተካሂደዋል።
በእነዚህ ቀናት የተመራጭ እጩዎች ግምገማ እና ልየታ ተከናውኗልም ብለዋል።
ከነሐሴ 5/2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም የጥሞና፣ የሹራ፣ የዱዓ እና መራጮች ለምርጫ ቀን የሚዘጋጁበት ቀናት መኾናቸውንም አስታውቀዋል።
ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም የዑለማዎች ምርጫ ይካሄዳል። ቀጥሎ ባሉት ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም እና ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶች እና የሠራተኛ ማኅበረሰብን የሚወክሉ ተመራጮች ድምጽ የሚሰጥበት ቀን መኾኑንም ተናግረዋል።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በዚህ ታሪካዊ ምርጫ ለቀጣይ አምስት ዓመታት መብት እና ጥቅሙን የሚያስጠብቁለትን ወኪል ካርድ ባወጣባቸው መስጅዶች በመገኘት ድምጽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ኢብራሂም ሙሐመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!