12ኛው የአፍሪካ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በጋና አክራ መካሄድ ጀመረ።

40
ባሕር ዳር: ነሐሴ 6/2017 ዓ.ም (አሚኮ)12ኛው የአፍሪካ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በጋና አክራ መካሄድ ጀመሯል። በመድረኩም የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽሕፈት ቤትኀላፊ አደም ፋራህ እና የብልጽግና ፓርቲ ሕዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኀላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ.ር) እየተሳተፉ ይገኛል። ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚካሄደው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ቀጣናዊ ትስስር፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ ሁሉን አቀፍ አስተዳደር፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሚና በአሕጉራዊ ልማት አጀንዳዎች ላይ ይመክራል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወፌ ሰንብታ ሰንብታ መጣች ለፍልሰታ”
Next articleተስፋ ሰጨው የወተት ልማት