
አዲስ አበባ: ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ቴክኖሎጅ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው።
በጉባኤው ከ18 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ፖሊሲ አውጭዎች የጤና ቴክኖሎጅ አልሚዎች እና የመንግሥት ተወካዮች የምርምር ተቋማት እየተሳተፉ ይገኛሉ። በጉባዔው መክፈቻው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስቴር የጤና ሥርዓት ኢኖቬሽን እና ጥራት መሪ ሥራ አሥፈጻሚ አባስ ሀሰን (ዶ.ር) ጉባኤው የጤናውን ዘርፍ ቴክኖሎጅ እና ኢኖቬሽን የሚያሳድግ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የጤና ፖሊሲ እና ቴክኖሎጅ ለማሳደግ በትብብር መሥራት እና የጤና ኢኖቬሽንን መተግበር አስፈላጊ እንደኾነም ገልጸዋል።
ዘጋቢ: አንዷለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!