የምሥራቅ ጎጃም ዞን የእንስሳት ተዋፅዖ አቅርቦትን ለማሳደግ እየሠራ ነው።

12
ደብረ ማርቆስ: ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት መመሪያ ባለፈው በጀት ዓመት የእንስሳት ምርታማነትን ለማሻሻል በተደረገው ጥረት የወተት ምርታማነትን በማሳደግ እና ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ በዘርፉ የተደራጁ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን አቅም ማሳደግ መቻሉን የመምሪያው ኀላፊ ዳኘ ዋሴ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቀንድ ከብቶችን ሳይንሳዊ በኾነ መንገድ አድልቦ በመሸጥ ማኅበረሰቡ በዘርፉ ተጠቃሚ እየኾነ መምጣቱን ገልጸዋል።
በዞኑ ከ700 ሺህ በላይ የአንድ ቀን ጫጩቶችን በማቅረብ የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ መሠራቱን የጠቆሙት ኀላፊው በዞኑ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተጀመረውን ዘመናዊ የዓሳ ርባታ ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል። ለእንስሳት ምርታማነት መጨመር የሚያግዙ ዘመናዊ የመኖ ማልሚያ ስልቶችን በማስፋፋት እና የእንስሳትን ጤና በመጠበቅ በዘርፉ ያደገ ውጤት ለማምጣት እየተሠራ መኾኑን ኀላፊው ተናግረዋል፡፡
ከመኖ አቅርቦትና የዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመሰረታዊነት የሚፈቱ የመኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች እየተገነቡ መኾኑንም ገልጸዋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ 24 የወተት ልማትና ግብይት ኅብረት ሥራ ማኅበራት እንደሚገኙ ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየሩዝ ምርትን ለማሳደግ ምን እየተሠራ ነው ?
Next articleየኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዘርፍን ለማዘመን የ25 ዓመታት የትራንስፎርሜሽን ኢኒሼቲቭ ይፋ ተደረገ።