የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር አለባችሁ። 

19

አዲስ አበባ: ነሐሴ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከሁሉም ከመላው ኢትዮጵያ ለተውጣጡ አዲስ ሠልጣኝ ሠራተኞች አቀባበል አድርጓል።

 

ሥልጠናው የሚሰጠው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሥተባባሪነት እንደኾነ ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ከሠልጣኞች ትንሿን ኢትዮጵያ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

 

እናንተን ከዚህ ለማድረስ ቤተሰቦቻችሁ እና ሀገራችሁ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል ያሉት ኮሚሽነሩ የተከፈለው ዋጋ ፍሬ አፍርቶ እዚህ በመደረሳችሁ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለሀገራችሁ እና ለእናንተ ምስጋና ይገባል ነው ያሉት።

 

በቀጣይ የሥራ ሕይወታቸው ስኬታማ ለመኾን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መኾን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

 

በሥነ ምግባር የታነጻችሁ፣ ሥራችሁን የምታከብሩ፣ የሚሰጣችሁን ኀላፊነት መወጣት የምትችሉ መኾን ይጠበቅባቹሃል ነው ያሉት።

 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ.ር) የሀገር ምሰሶ የኾነውን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን የምትቀላቀሉ ወጣቶች ከእያንዳንዱ ሰው ትምህርት የምትወስዱበት፣ ቀጣይ ተቋሙን የምትረከቡ እና የምታስቀጥሉ በመሆናችሁ ጠንክሮ መሥራት ይኖርባቹሀል ብለዋል።

 

የምትወስዱት ሥልጠና ብቁ ሠራተኛ እንደሚያደርጋችሁ እናምናለን ነው ያሉት። የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

 

ዘጋቢ: ሰላማዊት ነጋ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleያለበትን ሀገራዊ ኀላፊነት ለመወጣት እየሠራ መኾኑን የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ። 
Next articleለሻደይ በዓል የሚመጡ እንግዶች በአግባቡ ለማስተናገድ ዝግጅት ተደርጓል።