
አዲስ አበባ፡ ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሴት መሪዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ መልዕክት ከፍተኛ ሴት መሪዎች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፍራህ የሥራ ዕድል ፈጠራን ጨምሮ በሁሉም መስኮች የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተቋማዊ ማሻሻያዎች ተደርገዋል ብለዋል።
በቀጣይም ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት፣ የትምህርት እና ክህሎት ልማት ማላቅ እና የሴት መሪዎች ውሳኔ ሰጭነትን ለማሳደግ በትኩረት ይሠራልም ነው ያሉት።
የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር) መድረኩ በኢትዮጵያ የሚታዩ የተዛቡ ትርክቶችን በማረም የሴት መሪዎችን አቅም በሚገባ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል።
መንግሥት በለውጡ ዓመታት ለሴቶች መብት መከበር እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ውጤታማ ሥራዎች መሥራቱንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
በመድረኩ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለሴቶች ተጠቃሚነት ጉልህ አበርክቶ ለነበራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዕውቅና ተሰጥቷል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!