የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች አቀባበል ተደረገላቸው። 

74

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤልያስ አበበ ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በሰሜን ሸዋ ዞን መርሀቤቴ በገጠር ቀበሌዋች በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 533 ታጣቂ ወንድሞች ከነሙሉ ትጥቃቸው የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ገብተዋል ብለዋል።

ሰላምን የመረጡትን የሕዝብ ልጆች በፍቅር ተቀብለናል ነው ያሉት።

በባለፉት ጊዜያት ያሳለፉት ሕይወት እንዲያበቃ እና በቀጣይ ከመንግሥት ጋር ኾነው ሊሠሩ በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያም መምከራቸውን ተናግረዋል።

መሬት ያለው ዕውነት ሕዝቡ ሰላም ወዳድ እንደኾነ የሚያሳይ ነው ያሉት ኀላፊው ሕዝቡ አብዝቶ ሕግ እንዲከበርለት እንደሚፈልግም ገልጸዋል። ሕዝቡ ከመንግሥት ጎን መኾን ምርጫው መኾኑንም አመላክተዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ሕዝብ ሰላም ወዳድ፣ ሥርዓት የሚያውቅ፣ ዕውነትን የተረዳ እና አሰላስሎ የሚወስን መኾኑንም አንስተዋል። ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች እና ከመሪ ልጆቹ ጋር ኾኖ የተሟላ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ በትጋት እየሠራ ነው ብለዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ሕዝብ የሚፈልገው የሕዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች እንዲገነቡ፣ የሰው ሞት እንዲቆም፣ ሁሉም የሕዝብ አገልግሎት በተሟላ መንገድ እንዲጀመር፣ ትምህርት የናፈቃቸው ሕጻናት በነጻነት እንዲማሩ እና ሕዝብ እረፍት እንዲያገኝ መኾኑንም ተናግረዋል።

ይህም እንዲሳካ ቀሪ በጫካ የሚንቀሳቀሱ ወንድሞች ወደ ሰላም እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ከሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሰላም እንዲፈጠር እየሠሩ ላሉ የአካባቢው የሥራ ኀላፊዎች እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች ምሥጋና አቅርበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰላም አማራጭ የሌለው የጋራ ዕሴት እና ሃብት ነው።
Next article“ድሬዳዋ በታሪክ ገጽ”