በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት የኃይል አቅርቦት ተቋረጠ።

30
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት በመተማ፣ መተማ ዮሐንስ፣ ገለጎ አገልግሎት መዕከል እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጎንደር ሪጅን ከአዘዞ ወደ መተማ የሚሄድ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል አስተላለፊያ መስመር ላይ ብልሽት በማጋጠሙ ምክንያት ነው በመተማ፣ መተማ ዮሐንስ፣ ገለጎ አገልግሎት መዕከል እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦት የተቋረጠው።
በኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ ያጋጠመው ብልሽት ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በአከባቢው የሚገኙ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ሰላም እና ልማትን የሚያውኩ አካሄዶችን ለመከላከል አቅም ተገንብቷል” አቶ መሐመድ እድሪስ
Next articleሴቶች በማኅበራዊ እና በፖለቲካው ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል።