
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች ለመዲናችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱ፣ ደረጃውን የጠበቀ የክትመት ንጋት እና የማንሰራራት ዘመን አብሳሪዎች ናቸው ብለዋል።
ደረጃቸውን የጠበቁ ከተሞች የሀገራት ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ሚዛን ጥበቃ፣ የሕዝቦች የእሳቤ ከፍታ አድማስ እና አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚነበብባቸው ገጾች መኾናቸውን ገልጸዋል።አዲስ አበባ በልጇቿ ብርቱ ክንዶች እየለማችና እየደመቀች፣ በነዋሪዎቿ ትጋት እየፈካች እና እየተዋበች በተግባር ስሟን እየሆነች ያለች ከተማ ናት ነው ያሉት።
የሀገራችንና የአፍሪካ መዲናችን የውበት ብቻ ሳይሆን የቀልጣፋ አገልግሎት፤ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የምቹ ኑሮ፥ ከዚህም ባለፈ አጠቃላይ የሀገራችን ፈጣን ልማት የሚቃኝባት የዕድገታችን ማሳያ ናት ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን