
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሽዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ከሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በአካባቢው ሰላም እና ልማት ሥራዋች ዙሪያ መክረዋል።
በመድረኩ የወረዳው ሕዝብ ከሰላም ማስከበር ሥራው ጎን ለጎን የተጀመሩ የመሠረተ ልማት እና የመልማት ጥያቄዎች እንዲፈቱለት ጠይቋል። የሰሜን ሽዋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤሊያስ አበበ የሚዳ ወረሞ ሕዝብ ምርጫው ሰላም እና ብልጽግና መኾኑን አረጋግጧል ብለዋል።
ኀላፊው በተሠራው የሰላም ማስከበር ሥራ ብዙ ወጣቶች ከጫካ እየተመለሱ እንደኾነም ተናግረዋል።ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት የጋራ ኀላፊነት እንደወሰዱም አቶ ኤሊያስ አበበ ጠቁመዋል። የሚዳ ወረሞ ወረዳ የሰላም ተምሳሌት እንዲኾን የወረዳው ሕዝብ ሰላምን ለማረጋገጥ ከሠራው ሥራ በተጨማሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአካባቢው የጸጥታ ኀይል እና የወረዳው አመራር በቅንጅት መሥራታቸውን ኀላፊው አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን