የዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ተቋም ከ160 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

14
ደሴ: ነሐሴ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ተቋም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል፣ ወረባቦ፣ ተሁለደሬ እና ቃሉ ወረዳዎች ጋር በቅንጅት ዘላቂ ልማት እንዲመጣ እየሠራ ነው፡፡ግብረ ሰናይ ተቋሙ “የበጎነት ሳምንት” በሚል የአረንጓዴ ትግበራ ሳምንትን ታሳቢ በማድረግ በተሁለደሬ ወረዳ ከ160 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
እርስ በእርስ በመደጋገፍ ችግሮችን የጋራ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት የዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ፕሮግራም ማኔጀር ግዛው ገብረማርያም ናቸው። ድጋፉ በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንደይቀሩ የራስን ኀላፊነት ለመወጣት ያለመ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ አቶ ግዛው ከ160 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንደተደረገ ገልጸዋል። ድጋፉ በተለይም መጠለያ ላሉ ተፈናቃዮች በእጅጉ አስፈላጊ መኾኑን ነው የገለጹት፡፡
የተሁለደሬ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሰይድ አሕመድ ትምህርት ሀገርን ለማስቀጠል ዓይነተኛ መሳሪያ ነው ብለዋል። የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በወረዳው በትኩረት እየተሠራ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡ የዘላቂ ልማት መካነ ጥናት ተቋም በዘርፉ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ለማሟላት ያደረገው ድጋፍ ትርጉሙ ትልቅ ስለመኾኑም ጠቁመዋል፡፡ ሌሎች ድርጅቶች እና ግለሰቦችም በዚሁ በጎ ተግባር እንዲሳተፉ ጠይቀዋል፡፡የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፉን የተረከቡ አካላትም በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ትምህርት ቤት ይቀሩ የነበሩ ተማሪዎችን ችግር ለማቃለል ያግዛል ነው ያሉት። የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ: ደጀን አምባቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማዘመን እየተሠራ ነው።
Next articleነፍሰ ጡር እናቶች በወባ ሲያዙ ምን ማድረግ አለባቸው ?